Skip to content Skip to footer

የኦንላይን ዴቲንግ መዘዞች

በተለያዩ ሃገራት ይበልጥ ደግሞ እንደእኛ ከመንግስት ጥበቃ የሌለባቸው ሃገራት ላይ የኦንላይን ዴቲንግ ቀላል አይደለም። 

ለመተዋወቅ እና የሌሎችን ማንነትን በደንብ ለማጣራት ጊዜን መውሰድ፣ የግል መረጃን በቀላሉ አለመስጠትን ሁሌም ማስታወስ ያስፈልጋል::

ፎቶ እና የግል መረጃን በግልፅ መለዋወጥ በሚያስቸግርባቸው ሃገራት ላይ የኦንላይን ዴቲንግ ጥቃቶች ቁጥር ከቀን ወደቀን የከፋ ነው። ተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ ነኝ ብሎ የኩዊር ማህበረሰብን መከታተል እና መደብደብ፣ በማስፈራራት ገንዘብ መቀበል እንዲሁም በሌሎች ሃገራት ላይ ተጠቃሚን በማገት ከቤተሰብ ቀላል የማይባልን ገንዘብ መጠየቅ እየተለመደ የመጣ ነገር ነው።

ግራይንደር እና የመሳሰሉትን የዴቲንግ አፕልኬሽኖችን ሲጠቀሙ ከመቼውም በላይ ጥንቃቄን ማድረግ አንዘንጋ። ለመተዋወቅ እና የሌሎችን ማንነትን በደንብ ለማጣራት ጊዜን መውሰድ፣ የግል መረጃን በቀላሉ አለመስጠትን ሁሌም ማስታወስ ያስፈልጋል:: በተመሳሳይ ፃታ አፍቃሪ ጠል ሃገር ላይ የመንግስትም ሆነ የህዝብ ከለላ እንደሌለ በማስታወስ እያንዳንዱን እርምጃ በጥንቃቄ መራመድ ያስፈልጋል።

ከተለያዩ አጭበርባሪ አካውንቶች በማስተዋል እና በብልሃት ራስዎን ይጠብቁ።

Leave a Reply

Discover more from queerethiopia

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading