ለተወሰኑ ወራት ከዚህ በፊት አይተነው የማናውቀውን የጥላቻ ዘመቻ አይተናል። ምንም እንኳን የምንኖርበት ማህበረሰብ የተመሳሳይ ፃታ አፍቃሪ ጠልነቱን የምናውቅ ቢሆንም በቲክቶክ ይለቀቁ የነበሩ የዛቻ ቪድዮዎች ጥላቻው ምን ያህል ስር የሰደደ እንደሆነ አሳይተውናል።

በሙሉ ስማችን ወጥተን ኩዊር ማህበረሰብችንን መደግፍ ባንችልም፣ ከጎናችን ያሉ የተቃራኒ ፆታ አፍቅሪያን ወጥተው ስለእኛ በግልፅ መሟገት ባይችሉ ከስልኮቻችን ጀርባ ተከልለን የሰራነው ስራ እንደቀላል የሚታይ አይደለም። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተከታይ ያሏቸውን የቲክቶክ አካውንቶች ከማዘጋት እስከ ማስጠንቀቂያ ማሰጠት ድረስ በፅናት ታግለናል።
ትንሽ ናቸው እንዳሉን ሳይሆን ሺዎች ሆነን ተባብረን አሸንፈናል። ይህ “ዳይ ሪፖርት!” የተሰኘው ልዩ እትም እያንዳንዳችን የኩዊር ማህበረሰብ እና ደጋፊዎቻችን በነበረው እስከፊው ጊዜ እንዴት እንደተወጣነው ምስክር እና ማስታወሻ ይሆን ዘንድ የተዘጋጀ ነው።
በዚህች አጭር ማስታወሻ ውስጥ እንዴት ሪፖርት ማድረግ እንደተማማርን፣ በቀልድ በጨዋታ እያዋዛን እንዴት ጥላቻው ላይ እንደዘመትን እና እርስ በእርስ እንዴት እንደተጋገዝን ቅልብጭ አድርጋ ታሳየናለች።
የኩራት አንዱ መገለጫው ትብብር ነው:: ሳትደክሙና ሳትሰለቹ በአብሮነት ላደረጋችሁት ትብብር ሁሉ ምስጋናችን ይድሩሳችሁ።
ትግላችን ይቀጥላል!
(“ዳይ ሪፖርት!”ን ለማውረድ ወይም ለማንበብ ከታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ)