Skip to content Skip to footer

ከምናስበው በላይ የበለጠ የተገናኘን ነን

ደቡብ አፍሪካውያን በስርዓተ ጾታ ላይ የተመሰረተ ጥቃትን ለመቃወም ወደ ጎዳናዎች ሲወጡ፣ አገሪቱ ኃይለኛ እና ትልቅ የጋራ ሀዘንና እምቢተኝነት አይታለች ። ጥቁር የለበሱ ሰዎች የጠፉትን ህይወት ለማመልከት መሬት ላይ ተኝተው ነበር፣ ፕሬዝዳንቱም የስርዓተ ጾታ ላይ የተመሰረተ ጥቃትን ብሔራዊ አደጋ ብለው አወጁ። ነገር ግን ከተለቀቁ ቪዲዮዎች መካከል፣ በጥቁር ለባሾች መሀል ለእኔ ጎልቶ የታየኝ በቀስተ ደመና ባንዲራ የተጠቀለሉት ተቃዋሚ ነበሩ።

ያ ቀላል እንቅስቃሴ ብዙ የንቅናቄ ቦታዎች ትግላችን እርስ በርስ የተሳሰረ መሆኑን ለመግለፅ አሁንም ለመግለጽ የሚቸገሩበትን ነገር ያሳያል ብዬ አምናለሁ። በስርዓተ ጾታ ላይ የተመሰረተ ጥቃት የሚጠቁ ሰዎች ማንነታቸውን አይመርጥም። ሴቶችን፣ ወንዶችን፣ የኩዊር ማህበረሰብ እና በመካከላቸው ያለውን ሁሉ ይነካል።

ብዙ ጊዜ ማህበራዊ ችግሮችን እንደ የተለያዩ ክፍሎች እድርገን እናስባለን ማለትም የሴቶች መብቶች እዚህ ጋር የኩዊር መብት እዛ ጋር ፣ የኢኮኖሚ ፍትህ በሌላ ቦታ እያልን እናስባለን። ነገር ግን መሬት ላይ ሲወርድ፣ በእለት ተለት ህይወት ላይ፣ እነዚህ ችግሮች ይዋሃዳሉ። ጭቆና ይዋሃዳል። ኢፍትሃዊነት በተለያዩ ምድቦች ውስጥ ይፈስሳል። ለዚህም ነው ነፃነት ተመሳሳይ ነገር ማድረግ ያለበት።

በኬንያ የፋይናንስ ህግ ተቃውሞዎች ወቅት ያንን ተመሳሳይ ትስስር አይተናል። በተጠያቂነት እና ግልጽነት በሚጠይቁ ሰዎች መካከል፣ የቀስተ ደመና ባንዲራ እንደገና ትኩረትን የሚከፋፍል ሳይሆን ፣ እንደ ጎን ጉዳይ ሳይሆን፣ ኩዊር ሰዎች የህዝብ አካል፣ የትግሉ አካል እና ለፍትሃዊ የወደፊት ራዕይ አካል መሆናቸውን ለማስታወስ በድጋሚ አይተናል።

እውነቱም ቀላል ነው፤ እኛ የተገናኘን ነን። ደህንነታችን የተገናኘ ነው። ነፃነታችን የተገናኘ ነው። የወደፊት ዕጣ ፈንታችን የተገናኘ ነው። ሰዎች በስርዓተ ጾታ ጥቃት፣ ጦርነት፣ ሙስና ወይም ማንኛውንም ዓይነት ኢፍትሃዊነት ለመቃወም ሲነሱ፣ ለራሳቸው ብቻ ሳይሆን ለሚጎዱ ስርዓቶች ለተጎዱ ሁሉ እየታገሉ ነው።

ከደቡብ አፍሪካ ሴቶች፣ ከኩዊር ማህበረሰቦች፣ ከኬንያ ወጣቶች እና ከማንኛውም ዓመፅ እና ኢኩልነትን ከሚታገሉ ጎን! እናስታውስ ነፃነት አብሮነት ሲኖረው በጣም ጠንካራ ይሆናል።

Leave a Reply

Discover more from queerethiopia

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading