16 ቀን የሚቆየው የስርዓተ ፃታዊ ጥቃት ዘመቻ ከኅዳር 15- ኅዳር 30 በአለም አቀፍ ደረጃ የሚካሄድ ዘመቻ ነው። ይህም በይበልጥ በሴቶች ላይ የሚደርስን የተለያዩ ጥቃቶትችን በተለያየ ሚዲያ በማምጣት ለማህበረሰብ ግንዛቤ የማስጨበጫ ዘመቻ እና ለሚመለከተውም አካል “አንድ በሉን” የሚልን መልዕክት የማስተጋቢያ መድረክ ነው።

በአብዛኛው በይበልጥ ደግሞ እንደእኛ ያሉ ሃገራት ላይ ይህ ዘመቻ የእኛን እውነታ እና የህይወት ተሞክሮ ያካተተ አይደለም። ኩዊር ሰዎች እንደማህበረሰብ አባልነታቸው የራሳቸው የሆነ የህይወት ተሞክሮ አላቸው፤ ጥቃት ሲገጥም ታዲያ ለፖሊስም ሆነ ከጎን ላለ ሰው መንገሩ ለተጨማሪ ጥቃት ተጋላጭነን እንጂ መፍትሄ ወይም ፍትህን አያስገኝም።
ኩዊር ኢትዮጵያ በዚህ አለም አቀፍ ስርዓተ ፃታዊ ጥቃትን የመቃወም ዘመቻ ላይ የኩዊር ኢትዮጵያውያንን ህይወት ታሪክ እና የሚደርስባቸውን የተለያዩ ጥቃቶች ወደፊት በማምጣት <<እኛንም አዳምጡን፤አካቱን>> ትላለች። በዚህ 16 ቀን በሚቆየው ዘመቻ ላይ ከሌላው ማህበረሰብ እና በእኛው ማህበረሰብ የሚደርስ ጥቃትን፣ ጤናማ ግንኙነቶች፣ የስርዓተ ፃታ ሚና እና ሌሎችን በጥልቅ የምንወያይ ይሆናል።
እንደተለመድው ድምፃችንን በህብረት እናሰማ።
ትግላችን ይቀጥላል።