Skip to content Skip to footer

ንስንስ፡ የኩራት ገፅ እትም

እንኳን ወደ16ኛው የንስንስ እትም በሰላም መጣችሁ!

በዚህ እትም በማህበረሰባችን ውስጥ የሚገኙ በኢንተርኔት እና በአካል ህይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው ለመብታችን የሚታገሉ አክቲቪስቶችን ይዘን ቀርበናል፡፡ ለተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪዎች ትልቅ ጥላቻ ባለባት ኢትዮጵያ የማህበረሰቡ አባል መሆን ብቻውን አደገኛ ነው፡፡ ለመብታችን መታገልን መምረጥ ደግሞ የእነዚህን ታጋዮች ህይወት በይበልጥ ችግር ውስጥ የሚከት ነው፡፡ በኦንላይን ንቅናቁዎች እና ደህንነታቸው የተጠበቁ ቦታዎችን በማዘጋጀት፤ እንዲሁም አብሮነትን በመግለጽ እነዚህ ጽኑ ግለሰቦች ጥንካሬያቸውን ከማሳየት በተጨማሪ ለውጥን ለመፍጠር የሚደረግን ተጋድሎ የሚያሳዩ ምሳሌዎች ናቸው፡፡ መስዋእትነታቸው ተቀባይነትን እንድናገኝ እና ራሳችንን መቀበል እና የማህበረሰብ ድጋፍ ራሱን የቻለ ንቅናቄ መሆኑን ያሳያል፡፡

ይህ የንስንስ እትም ዘግይቶ በመውጣቱ ይቅርታ እየጠየቅን፤ ለትግስታችሁ ልናመሰግን እንወዳለን፡፡ እነዚህን ብርቱ ምስክርነቶች እንድታነቡ ስንጋብዛችሁ በደስታ ነው፡፡ 

በ*etqueerfamily@gmail.com  ልታገኙን ትችላላችሁ፡፡

Leave a Reply

Discover more from queerethiopia

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading