Skip to content Skip to footer

መጋለጥ እና ርህራሄ

በተደጋጋሚ በሚለቀቁ ቪዲዮዎች ሰዎች ሲሳለቁበት እያየሁ ልቤ በጣም አዘነ። በእነርሱ ጎጂ አስተያየቶች አራዳ ወይንም ብልህ እንደሆኑ አድርገው በማሰብ ወንዶችን  ይወዳል ወይም ቀሚስ ለብሶ ተገኝተዋል በሚል ልባቸው እስኪጠፋ ያፌዙበታል። አንዳንዱ ደግሞ እሱ ራሱን በመሆኑ ብቻ ወጋችንን፣ ባህላችንን እና ሃይማኖታችንን እንደ”ተሳደበ”  በመሰብ ይታሰር ወይም ይባስ ብለው ይገደል ብለው ይፎክሩበታል።

እሱ የተመሳሳይ ፆታ አፍቃሪ፣ ከሁለትዮሽ የፆታ ስራዓት ውጭ፣ ባይሴክሹዋል ወይም ሌላ ነገር እንደሆነ አላውቅም ፣ ግን እኔ በእርግጠኝነት የማውቀው የህዝብ ጠላት ቁጥር አንድ የሚል ስያሜ እንደተሰጠው ነው። እንደ እውነቱ ከሆነ እራሳችንን ስለሆንን ብቻ ልንታሰር እንደምንችል ሳስብ ያስፈራኛል። ህብረተሰቡ “የተለመደ” ለሚለው ጠባብ ፍቺው የማይስማማውን ማንኛውንም ሰው ሊያንገላታ እንደሚችል ማስታወሻ ነው፤ ይሄ መሆኑ የሚያሳዝን ነገር ቢሆንም።

ተደብቆ፣ ታስሮ ወይም ታድሎ ከሀገር ወጥቶ ሊሆን ይችላል። ለእሱ ሲል፣ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደሌለ ተስፋ አደርጋለሁ። ራሱን ለመሆን በመድፈሩ ብቻ ተሳዶ ቤቴ ከሚላት አገሩ ለቆ ለመውጣት በመገደዱ ጥልቅ ሀዘኔታ ይሰማኛል። የትም ብትሆን ደህንነት የተጠበቅ እንደሆነ ተስፋ አደርጋለሁ። ደህና እንደሆንክ እመኛለሁ። አይዞህ የሚልህ ደጋፊ ማህበረሰብ እንደምታገኝ ተስፋ አደርጋለሁ ምክንያቱም ይህች ሀገር ለየት ላልነው ለኛ ህይወትን አስቸጋሪ ለማድረግ የቆረጠች ይመስላል።

ትግል ከሁላችንም ጋር የተቆራኘ በመሆኑ ጥላቻንና ለማጥፋት በጋራ መቆም እንዳለብን ያስታውሰናል። በርትተህ ኑር፤ በዚህ ውጊያ ውስጥ ብቻህን እንዳልሆንክም እወቅ። ከጎንህ ነኝ።

Leave a Reply

Discover more from queerethiopia

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading