አስረኛው የንስንስ እትማችን ለንባብ በቅርቡ እንደምትበቃ ስንነግራችሁ በደስታ ነው። ይህ እትም “ውይይት” የሚል ርዕስ ያለው እና በኩዊር ማህበረሰባችን ውስጥ ያሉትን ውስብስብ ችግሮች የሚዳስስ ሲሆን ማህበረሰባችን እራሱን የሚገልፅበት እና እራስን ለመቀበል ደህንነቱ የተጠበቀ ቦታዎችን ቢያቀርብም ያልተመረመሩ አድሎአዊ ጉዳዮችን እና ሊታረሙ የሚገቡ መርዛማ ነገሮችንም ሊይዝ ይችላል።

ይህ ውስጣዊ እይታ እራሳችንን እንደ ማህበረሰብ አጥብቀን እንድንጠይቅ አስችሎናል። ከመረመርናቸው ጥያቄዎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡ እነዚህን ጉዳዮች በማህበረሰባችን ውስጥ እንዴት እንቃኛለን? አባላቱን ተጠያቂ የሚያደርግ ጠንካራ የኩዊር ማህበረሰብ እንዴት ማፍራት እንችላለን? ኩዊር ማህበረሰብ ውስጥ ሆነው ከተገለሉት ሰዎች ጎን እንዴት ነው የምንቆም ?
በግልጽ ንግግሮች ውስጥ የሚሳተፍ እና በእኛ ኩዊር ማህበረሰብ ውስጥ ያሉትን መርዛማ ነገሮች የሚመረምረው ይህ የንስንስ እትም እንዳያመልጥዎት። በLGBTQ+ ማህበረሰብ ውስጥ ባሉ ጎጂ ወሬ፣ ሐሜት፣ የአደንዛዥ ዕፅ አጠቃቀም፣ አድሎአዊነትን እና የተገለሉ ማህበረሰቦች ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ጨምሮ ስለ ብዙ ጉዳዮች በግልፅ እንነገገራለን።
እነዚህ ውይይቶች ጠንካራ እና ጤናማ የኩዊር ማህበረሰብ ለመገንባት አስፈላጊ ናቸው። ውይይቱን እንደምትቀላቀሉ ተስፋ እናደርጋለን።