
ማንነትሽን መሰረት ያደረገ አስቂኝ ገጠመኝ አለሽ?
“ከትንሽ ጊዜ በፊት ኩዊር መሆኔን የነገርኳት ጓደኛዬን አገኘኋት። እሷ አሁንም የኔን ኩዊርነት ለመቀበል ገና እየሞካከረች ነው፣ ነገር ግን በትክክል ይሄ ማንነቴ የሚያልፍ ምዕራፍ እንዳልሆነ ታውቃለች! ለማንኛውም፣ በውይይታችን ወቅት፣ በዘፈቀደ እንዲህ አለች፣ “ስለዚህ አሁንም የወንድ ጓደኛ አላገኘሽም? በትክክል ስለማግባት እና ስለመውለድ ማሰብ አለብሽ!” እኔም “በጣም ደስታ የሚሰጠኝ ግንኙነት ውስጥ እንዳለሁኝ ታውቂያለሽ አይደል?” አልኳት። 😂 በይ መጨረሻውን ልንገርሽ “እንዲያውም ግንኙነቱ ውስጥ ቦይ ፍሬንድ እኔ ነኝ ብያት አረፍኩ!” በርግጥ ነገሮችን ትንሽ ወሰብሰብ አድርጎታል … አስቸጋሪ ነገርም ነው ግን ዋጋ ያለው ትግል ነው ሰለ እውነት አንዳንድ ሰዎች አይረዱትም፤ ግን ይህን አስደሳች ህይወቴን እየኖርኩ ያለሁበት ጊዜ ነው።💃✨” – ጆይ