
በምስራቅ አፍሪካ ኩዊር መሆን ከባድ ነው። የኩዊር አክቲቪስት መሆን የበለጠ ከባድ ነው። ብዙ አደጋዎችንም ያስከትላል እንደ ከቤት መባረር፣ ድብደባ፣ “የማስተካከያ” መደፈር ሰለባ መሆን እና መገደልን ያስከትላል።
እንደ አክቲቪስት የእኛ የኩዊር ሰዎችን መብት ለማስከበር የምናደርገው እንቅስቃሴ ሊጎዳን እንደሚችል ተረድቻለሁ ነገር ግን ዝም ማለት አማራጭ ስላልሆነ እንቅስቃሴያችን በቁርጠኝነት እንቀጥላለን።
ኡጋንዳዊው ታዋቂ የኤልጂቢቲኪው አክቲቪስት ፍራንክ ሙጊሻ ይህን ለመብት ትግል መቆምን በምሳሌነት ያሳያል። ኩዊር መሆን በኡጋንዳ ማህበረሰብ ተቀባይነት ባይኖረውም፣ ለሞት ጥቃት ወይንም በግድያ ማስፈራሪያዎች የማይዳርግበት ጊዜን ያስታውሰናል። ኡጋንዳ ለኤልጂቢቲኪው ሰዎች እየከፋች በመጣች ቁጥር የእሱም የበለጠ ለመብታችን የመታገል አቋሙ እየጠነከረ መጥቷል።
በአፍሪካ ውስጥ ባለፉት ጥቂት አመታት ውስጥ ብዙ ሆሞፎቢክ ህግጋት የወጡ ሲሆን ጋና እና ዩጋንዳ ሁለት ምሳሌዎች ናቸው። ይህ ጊዜ እኛ አፍሪካውያን ኩዊሮች ለመብታችን ለመቆም የምንችለውን ሁሉ የምናደርግበት ነው። ይሄም የራሱ አደጋዎች እንዳሉ ግልፅ ነው። እንደ ፍራንክ ሙጊሻ ያሉ ሰዎች ግን እንደሚቻል ያሳዩናል። እንደ ኢትዮጵያዊ የኩዊር ታጋይ ኩዊር ማህበረሰቤን ነፃ ለማውጣት የበኩሌን ሚና መጫወት እንዳለብኝ ተስፋ ይሰጠኛል።
በታይም “የ2024 ከፍተኛ ተደማጭነት ያላቸው 100 ሰዎች” መካከል በመመረጡ ኩራት ይሰማኛል። እንኳን ደስ አለህ ፍራንክ ሙጊሻ። ለሁላችንም የተስፋ ብርሃን መሆንህን እንደምትቀጥል አልጠራጠርም።