Skip to content Skip to footer

ኩራት እና የቤተሰብ ራስን መግለጥ

የእህቴ ልጅ ሌዝቢያን እንደሆነች ስትነግረኝ፣ ስላመነችኝ ደስታ ተሰማኝ። እኔ ሌዝቢያን ነኝ ቤተሰቦቼም ያውቃሉ፣ ይህም ማንነቷን እንድትነግረኝ ደህንነት እንዲሰማት አድርጓታል።

አባቷ ብዙውን ጊዜ ስለ ጌይ ሰዎች አሉታዊ ነገሮችን ይናገራል። ለእሱ ወይም ለእናቷ ገና ለመንገር ዝግጁ አይደለችም ይህም ምንም ችግር የለውም። እኔ ግን ጆሮዬን ሰጥቼ እንደምሰማት ታውቃለች። ምን እንደሚሰማት፣ ስለተጨነቀችበት ነገሮች እና አይታ ስለወደደቻቸው ሴቶች ነገረችኝ። እኔም ብቻዋን እንዳልሆነች እንድታውቅ የራሴን ታሪኮች ነገርኳት።

ስለማነነቴ ግልጽ መሆኔ በጣም አገዟታል። ራሴን ስለተቀበልኩ ያለ ጥርጥር ድጋፍ እንድሆናት አስታዎፅ አድርጓል። ኩራት ክብረ በዓል ብቻ አይደለም – ለራሳችን በሃቅ መኖር ማለት ነው፤ በተለይ ደግሞ ሁኔታዎች ከባድ ሲሆኑ። የኛ በዛ ሁኔታ መኖር ሌሎችም እራሳቸውም መሆን እንደሚችሉ ያሳያቸዋል።

አንድ ቀን ለወላጆቿ ልትናገርም ላትትናገርም ትችላለች። ዛሬ ላይ ግን ምንም ቢሆን የሚደግፋት ሰው እንዳላት ታውቃለች። ለእኔ ኩራት ማለት ይህ ነው፡ ለሌሎች ደፋር እንዲሆኑ ቦታ መፍጠር።

ዛሬ ላይ ግን ምንም ቢሆን የሚደግፋት ሰው እንዳላት ታውቃለች። ለእኔ ኩራት ማለት ይህ ነው፡ ለሌሎች ደፋር እንዲሆኑ ቦታ መፍጠር።

Leave a Reply

Discover more from queerethiopia

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading