በየአመቱ ግንቦት ፰ ኃይላችንን፣ ጽናታችንን እና ውበታችንን ለማክበር በአንድነት የምንቆምበት ቀን ነው። ብዙ ጊዜ ዝም ሊያሰኘን፣ ሊያሳፍረን ወይም እንደሌለን ለማድረግ በሚሞክር ዓለም ውስጥ፣ ያለይቅርታ መኖራችንን፣ መውደድን እና ማደግ እንቀጥላለን። በእያንዳንዳችሁ ምን ያህል ኩራት እንዳለኝ ልነግራችሁ እፈልጋለሁ ፤ መኖር በመቀጠላችሁ፣ በመቃወማችሁ፣ በማለማችሁ ፣ እና አለም ለእኛ ባይቆምም እርስ በእርስ ለምናሳየው ህብረትና መረዳዳት ።

ማንነትሽን ለሌሎች ያሳወቅሽ ብትሆኚ፣ ማንነትህን እየመረመርክ ብትሆን፣ በዙሪያዎ የሚደግፉ አጋሮች ቢኖርዎት፣ ቤትሽ ከስልክ ሰሌዳው ጀርባ ተደብቀሽ ወይም አሁንም መንገድህን እየፈለግክ ቢሆን የኩዊር ማህበረሰቡ አካል ናችሁ። እርስዎ የተወደዱ ኖት። ብቻችሁን አይደላችሁም።
እንደኩዊር ኢትዮጵያውያን በተለይም በማህበራዊ ሚድያ ላይ ጥላቻ በቀላሉ ሊሰራጭ የሚችል ፈተናዎች ቢያጋጥሙንም አሁንም መበርታታን ቀጥለናል። የኛ ጽናታችን በሕይወት ለመትረፍ ብቻ ሳይሆን ደስታን ለመፍጠር፣ የተመረጡ ቤተሰቦችን በመገንባት እና አስተማማኝ የምንሆንበትን ዓለም ተስፋ በማድረግ እና በመታገል ላይ ነው። ስለዚህ ዛሬ እና በየቀኑ እኛነታችንን አከብራለሁ። አሁንም አለን። አሁንም እንኮራለን። አብረን መነሳታችንንም እንቀጥላለን።