Skip to content Skip to footer

የቫቲካን የእምነት ጉዞ እና LGBTQ+ ሰዎች ተስፋ

የLGBTQ+ ሰዎች በሃይማኖታዊ ማህበረሰቦች ውስጥ መቀበል ለማግኘት በውጣ ውረድ የተሞላ ጉዞ ነው፣ ነገር ግን የቅርብ ጊዜ ክስተቶች ተስፋ ሰጥተውኛል። እ.ኤ.አ 2025 ለLGBTQ+ ክርስቲያኖች እና ደጋፊዎቻቸው የተዘጋጀው የቫቲካን ጉዞ ትልቅ እርምጃ ነው። ይህ የሚያሳየው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ለሁሉም ሰው እንግዳ ተቀባይ ቦታ ሊሆን እንደሚችል ነው።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ላይ በጎ ተጽዕኖ እንዳሳደሩ ብዙ ጊዜ ይሰማኛል። እግዚአብሄር ሰዎች የፈለጉትንም ቢወዱ እና ሰው ምንም ቢሆን እሱ እንደሚወደን ብዙ ጊዜ ያስታውሱናል። የሳቸው መልእክት LGBTQ+ ግለሰቦችን ጨምሮ ሁሉንም ሰው የምታቅፍ የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን እንድናስብ ያበረታታናል።

ለእኛ እንደ ኩዊር ኢትዮጵያውያን ይህ የእምነት ጉዞ ልዩ ስሜት እንዲሰማን ያደርጋል። በማንነታችን መኩራት እንደምንችል የሚያሳይ ምልክት ነው። ስለ LGBTQ+ ጉዳዮች በግልፅ መናገር ባንችልም እምነታችንን ከስሜታችን ጋር ማስታረቅ እንችላለን ይህም ስሜትም ብዙ ጊዜ ብቸኝነት ለሚሰማቸው ሰዎች አስፈላጊ ነው። ፍቅር ጥላቻን ያሸንፋል የሚለው ሃሳብ ለኛ አስፈላጊ ነው፣ ምክንያቱም ዋጋ ሊሰጠን እንደሚገባ ያሳታውሰናል።

ይህ ጉዞ ተስፋን እና ጥንካሬን ሊያበረታታ ይችላል፣ ይህም በእምነታችን ስፍራችን ተቀባይነትን እንደምናገኝ እንዲሰማን ይረዳናል። እናም እኛ እንደ ኢትዮጵያውያን ኩዊሮች አንድ ቀን በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ነፃነት እና ተቀባይነት ልናገኝ እንደምንችል እንዳምን አድርጎኛል።

Leave a Reply

Discover more from queerethiopia

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading