Skip to content Skip to footer

የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ጠልነት እምቢ ማለት (አልመማር/መተው)

ኢትዮጵያ ውስጥ ስለተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪያን ገና ከልጅነት ጀምሮ ስህተት እንደሆነ ተምሬያለሁ:: ከዚህ የተለየ ነገር እንደሰማሁ አላስታውስም:: ሁሉም ነገር በጥቁርና ነጭ ለብሶ ይቀርብልናል በግልፅ መስመር የተደረገባቸው  ልክ እና ስህተት የሚባሉ ነገሮች አሉ::  ትልልቅ እህትና ወንድሞቻችን እንኳን ሳይቀር መደበኛ ከሚባል ውጪ በሆነ ነገር ላይ ጥላቻ ነበራቸው:: እርግጥ ነው፣ ሃይማኖታዊ አመለካከቶች በዚህ ረገድ ሚና ተጫውተዋል። ነገር ግን ወንድሞች እና እህቶች አርአያዎቻችን ነበሩ፣ እናም የሚሉንን ሁሉ ያለ ጥርጥር በልባችንን እንቀበላለን። ሁሉም ነገር የተቀየረው የቅርብ ጓደኛዬ ስለ ማንነቷ በግልፅ ስትነግረኝ ነው:: ለኔ አጋጣሚው በጣም አስተማሪ ነበር:: የማውቀው የመሰለኝን ብዙ ነገር እንድፈትሽ አድርጎኛል፤ ያ ጓደኝነት በእውነት ለእድገቴ ትልቅ አስተዋጽኦ አድጓል።

መተማመንን ስላስተማረኝ ጓደኝነታችን በጣም እየጠነከረ መጣ። ራስን መሆን አደጋ ላይ በሚያስጥልበት እና የብቸኝነት ስሜትን በሚፈጥርበት ቦታ ላይ ጓደኛዬ  አምና  ስለነገረችኝ ይበልጥ አቀራረብን፤ ስለሷ የሚሰማኝን ነገር በጭራሽ አልቀየረውም ይልቁንም አምናኝ ስለነገረችኝ በጣም ደስ አለኝ። በእህትና ወንድሞቼ እይታ ላይ ጥገኛ አይደለሁም፤  አሁን ትልቅ ነኝ እና ለራሴ ማሰብን ተምሬያለሁ። ነገሮችን በተለየ መንገድ የተረዳሁት በዚህ መንገድ ነው። ወላጆች እና ማህበረሰብ የሚያስተምሩትን ሁሉ መቀበል የለብንም። ልጅ  ስትሆን ብዙውን ጊዜ የራስ አስተያየት እንዲኖርሽ  ትፈሪያለሽ፤ ነገር ግን ከጊዜ በኋላ ያንን ፍርሃት መተው ትማሪያለሽ። ዓለም የሚጥልብኝን ሁሉ የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ጠልነት ጭምር መቀበል አቆምኩ። ያመንኩበትን ነገር  ለምን ብዬ  መጠየቅ ጀመርኩ።

ዛሬ ላይ ያሉ ወጣት የተመሳሳይ ጾታ አፍቃሪ ጠሎች አይገቡኝም። የወላጆቻችን ትውልድ መረጃዎች ስለሌሉ ብለን ልናስታርቀው እንችላለን። አሁን ላይ ግን መረጃዎች በእጆቻችን ላይ ናቸው፤ ጥላቻን መምረጥ ደግሞ ጭራሽ የማይገባኝ ምርጫ ነው። የሃይማኖት አመለካከቶችን ላከብር እሞክራለሁ ግን የሰዎች መብትስ?  ለምንድን  ነው ከእኛ በተለየ ሁኔታ ፍቅርን እና  ግንኙነቶችን ስለሚኖሩ ሰዎች የምንንገበገበው?

የራሳችን ጉዳይ ላየ ማተኮር እና ከሌሎች ጋር በደግነት እንድንመላለስ ተስፋ አደርጋለሁ። እስከ መጨረሻው ድረስ መማር፣ እይታን በተሻለ መቀየርን  እና ድጋሚ መማርን እንቀጥል።

Leave a Reply

Discover more from queerethiopia

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading