Skip to content Skip to footer

የኩዊር ፍቅር አስተማማኝ ባልሆነ ቦታ

የቫለንታይን ቀን ደርሶል፣ ይሄም የተደባለቀ ስሜት እንዲሰማኝ አድርጎኛል። ከፍቅረኛዬ ጋር ፡ አበባ፣ ቸኮሌት እና ለእኔ እና ለእሷ ትርጉም ያላችውን ነገሮች እየሰጠኋት ለማክበር በጣም ጉጉት ላይ ነኝ። አብረን ሆነን ጥሩ እራት የምናበስልበት እና የምንፈልገውን ፊልም የምናሳይበት የራሳችን ቤት አለን። ቀኑ በፍቅር የምናሳልፈው እና ለገነባነው ነገር ሁሉ ኩራት የተሞላ እንዲሆን በጣም እፈልጋለሁ።

ነገር ግን ይህ ቀን ጭንቀትንም ቋጥሮ ነው የሚመጣው። አበባ ለመግዛት ስሄድ፣ ለማን እንደሆኑ መዋሸት አለብኝ። የአንዲት ሴት የቫለንታይን አበባ መግዛት የተለመደ ነገር አይደለም፡ ሴቶች አበባ እንዲቀበሉ እንጂ እንዲሰጡ አይጠበቁም። በተለይ አብረን ስለምንኖር ወደ ቤት አበባ ስወስድ የተወሰነ እጨነቃለሁ። አስቀድሜም አስባለሁ። ሰው ምናልባት ሊጠይቀኝ ይችላል ስለዚህ አስቀድሜ የሆነ ምክንያት ማዘጋጀት አለብኝ። አድካሚ ነገር ነው። ቀኑ ስለ ደስታ እና ፍቅር ብቻ ቢሆን እመኛለሁ፣ ግን በምትኩ ይህንን ጭንቀት ተሸክሜያለሁ።

ኩዊር ሰዎች በሚጠሉባት ኢትዮጵያ ውስጥ ኩዊር ሴት መሆን ይሄ ነው። ያለምንም ፍራቻ በግልጽ ብወዳት ደስ ይለኝ ነበር። ግን ምንም ከባድ ቢሆንም የምትሰጠኝን ደስታ እወደዋለሁ።

ስለዚህ መልካም የቫለንታይን ቀን። እኔ በምፈልገው መንገድ ማክበር ላልችል እችላለሁ፣ ነገር ግን አሁንም በህይወቴ ውስጥ ስላለችኝ በጣም ደስተኛ ነኝ።

Leave a Reply

Discover more from queerethiopia

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading