ኩዊር መሆኔ በዕለት ተዕለት ሕይወቴ ውስጥ ብዙ ሚና አይጫወትም። በእውነቱ ኩዊርነቴ የማንነቴ አንድ በጣም ትንሽ ነው። የእኔ ወሲባዊ ምርጫ ወይም ዝንባሌ የህይወቴ አንድ ትንሽ ክፍል ብቻ ነው። ጓደኞቼ እና በዙሪያዬ ያሉ ሰዎች ጥሩ ናቸው። በኩዊርነቴ ምክንያት በተለየ መንገድ አያዩኝም፣ አያገሉኝም ወይንም ስለ እኔ ኩዊር መሆንም ምንም አይነት ግድ የላቸውም። ወደ ቤተሰቤ መጥቼ ስለ ኩዊርነቴ ከነሱ ጋር ብወያይ ትልቅ ጉዳይ ሊሆን ይችላል ብዬ አስባለሁ። ስለ ጥላቻ ደግሞ ብዙ ሰዎች ብዙ ነገሮች ዝም ብለው ይጠላሉ። ስለዚህ ይሄ የዚህን ያህል እንዲረብሸኝ አልፈቅድም። በዙሪያዬ ያሉትን ሁሉንም ጥላቻዎች ችላ በማለት ህይወቴን ብቻ እኖራለሁ።