ባለፈው ሳምንት መጨረሻ፣ ከኩዊር ሰዎች ጋር አሪፍ የሆነ ጊዜ አሳለፍኩ። ይህንን እድል በማግኘቴ አምላኬን ሳመሰግን ከመዋሌም በላይ በጣም በትልቅ ደስታ ተውጬ ነበር።
እዛ ስብስብ ላይ ስገኝ ምንም እንኳን ሁሉም ሰው ጓደኛዬ ባይሆንም እና አንዳንዶቹ እንደውም አይቻቸው የማላውቃቸው ሰዎች ቢሆኑም በቀኑ መጨረሻ ከሁሉም ጋር ጠንካራ ግንኙነት እንደ መሰረትኩ ነው የተሰማኝ። ስዚህም ከሁሉም ጋር ያለምንም መሳቀቅ ብዙ ታሪኮቻችንን እና ልምዶችቻችንን አውርተናል።
ስለ ሁሉም ነገር ተነጋገርን፤ ስለ ወሲብ፣ ዴቲንግ፣ ሥራ እና በየቀኑ የኅጝቭጥቕ+ ሰዎች የሆንን ሰዎች ስለ የሚያጋጥሙን ነገሮች እያነሳን ተነጋገርን። በተለይ እኛ በነፃነት መኖር በማንችልበት አገር ላይ እንደዚህ ስንሰበሰብ ነፍሴን ነው ያደስኳት። እራሳችንን ለመሆን እና አእምሯዊ ደህንነታችንን ለመንከባከብ አስተማማኝ ቦታዎች እንዴት እንደሚያስፈልጉንም የበለጠ አውቀናል።
ቆሻሻ እና የማንፈለግ እንደሆንን በተደጋጋሚ በሚነግረን ህብረተሰብ እና ዓለም ውስጥ እንደምንኖር ሰዎች፣ እንደኛ ኩዊር በሆኑ ሰዎች መከበቡ መንፈስን የሚያድስ ነበር። ስቀናል፣ ጭንቀታችንን ተካፍለናል፣ እና ለእርስ በርስም ድጋፍ ሰጠተናል። የመረጥነው ቤተሰባችን ምን ያህል ዋጋ እንዳለው እና አንዳችን በሌላው ውስጥ ምን ያህል ጥንካሬ እንደምናገኝ አስታወሷኛል።
ተስፋ እና የበለጠ የመቆራኘት ስሜት እየተሰማኝ ነው የዋለው። አንድ ላይ ለፈጠርናቸው አስተማማኝ ቦታዎች አመስጋኝ የሚያደርጉኝ እንደነዚህ ያሉት ጊዜያት ናቸው። የሚቀጥለውን ሃንግአውትን በጉጉት በመጠበቅ ላይ ነኝ!