Skip to content Skip to footer

ኩራት፡ የእህት እምነት

እህቴ አዘውትረው የሚገናኙ ወንዶች ብቻ ያሉበት ጀማ አላት። ከመካከላቸው አንዱ ከሌሎቹ የበለጠ ሃይማኖተኛ ነው እናም የዚ ጀማ አባል መሆኗ እና ብዙ የወንድ ጓደኞች መያዟ ስህተት እንደሆነ ብዙ ጊዜ አስተያየት ይሰጣል። እንደተለመደውም ይህንን አስተያየቱ በቅርብ መልሷ ይደግመውና እንደውም ከወንዶች ጋር ብዙ ጊዜ የምታሳልፍ ከሆነ ሌዝቢያን ስለሆነች እንደሆነም ጭምር ያክልበታል፤ ብዙ የሴት ጓደኞች ማፍራት እንዳለባት ይነግራታል። እሷም እየሳቀች ሌዝቢያን መሆን ከወንድ ጓደኞች ማፍራት ጋር ምንም ግንኙነት እንደሌለው ትነግረዋለች። ከወንድ ጓደኞቿ መካከል አንዳቸውም ከየትኛውም የፍቅር ጓደኝነት ከመሰረተቻቸው ወንዶች ጋር አይተዋት አያውቁም። ይህም አንዳንዶቹ ሌዝቢያን ናት የሚለውን ግምት ሊጋሩ እንደሚችሉ እንድታስብ አድረጓታል። ግን ልጁ ይህንን ሲል የሰሙ የተወሰኑ ጓደኞቿ የማያገባው ነገር ውስጥ እንዳይገባ ነገሩት። እሷ የተቃራኒ ፆታ አፍቃሪ ስለመሆኗ ተናግራ ራሷን መከላከል እንደማትፈልግ ተሰምቷታል። ይልቁንም ከሁሉም በላይ ሌዝቢያን መሆን ምንም ስህተት የለውም ብላ ታምናለች። እንደውም እሷ እንደሆነች ከገመቱም የራሳቸው ጉዳይ ነው ብላለች። በማንነቷ የምትተማመን እህት በማግኘቴ ኩራት ይሰማኛል፣ በግምታቸው የማተጨነቅ! የብዙዎቻችን እህቶች እና ወንድሞች እንደዚህ እንዲሰማቸው ተስፋ አደርጋለሁ። ይህ ለእኔ የኩራት ወር ስጦታዋ ነው።

Leave a Reply

Discover more from queerethiopia

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading