Skip to content Skip to footer

ድሮ እና ዘንድሮ

ልጆች እያለን ራስን ለማወቅ ያለው ጉጉት ትልቅ ቢሆንም ምንጭ ግን አይኖርም። በአካባቢያችን “ያ ነገር” እየተባለም አይወራም፣ ሚዲያው ትኩረት ሰጥቶት አይወራም። የብቸኝነት ስሜቱ ከባድ ነው፤ በከተማው ሰሜቱ ያላችሁ እናንተ ብቻ እንደሆናችሁ ታስባላችሁ። እድሜ ከፍ እስከሚል ድረስ እንድናንተ ያለውን ለማግኘት ቀላል አል ነበረም። ሀይማኖተኜነቱ ደግሞ ነገሮችን ያባብሳሉ፤ ከፈጣሪም ከሰውም ተደብቃችሁ እንድትኖሩ ተፅዕኖ ይፈጥራሉ። 

ታዲያማ የዛሬን የወጣት ጉዞ ሳይ እኮራለሁ። ቢያንስ ቢያንስ “ሌዝቢያን” ወይም “ጌ” ብለው በአማርኛ ቢፈልጉ በእኛው ለእኛው የተፃፉ ብዙ መረጃዎችን ያገኛሉ። ከተማ ቀመሱ ብቻ ሳይሆን በየገጠሩ ያለው የኩዊር ማህበረሰብ ራሱን መሳይ በቀላሉ በማህበራዊ ሚድያው ማግኘት ይችላል። አንድ ራሷን እየፈለገች ያለች ኩዊር ሴት ከሌሎች ልምድ መውሰድ የሚረዳትን ታሪኮች ማንበብ ትችላለች።  ማህበራዊ ሚድያው በጥላቻ የተበረዘ መንደር ቢሆንም ለአዲሱ እና ለሚመጣው ትውልድ የራስን ፍለጋን ጉዞ የተሻለ ማድረጉ አይካድም። እኛን የሚመስሉንን ከማወቅ ባለፈም፣ ጓደኝነትን፣ ፍቅርን እና ህብረትን እንድንመሰርት እረድቶናል:: 

በተለያየ እምነት ውስጥ ሆነን መኖር እንደምንችልም ኩዊር ሆነው በቤተ እምነቱ ከሚያገለግሉ መማር ችለናል። “ያ ነገር” እየተባለ በየሰፈሩ መወያያ መሆኑ አስጊ ቢሆንም እንደእኔ ግን የለውጡ ጉዞ ነው እላለሁ። ለውጥ የሌለ ይመስላል ለውጥማ አለ። ይኸው እንዲህ እየተፃፃፍን በመኖር እያሸነፍን አይደል?! 

መኖራችንን እንቀጥላለን

Leave a Reply

Discover more from queerethiopia

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading