Skip to content Skip to footer

ወደ ድብቅ ቦታዎች ማፈግፈግ

ኩዊር ማህበረሰባችንን እና በፊት የነበረውን ጊዜ እያሰብኩ አዘንኩ። ከጥላቻ ዘመቻው በኋላ ብዙ ራሳቸውን መሆን የማይፈሩ፣ አካባቢያችን ላይ የምናያቸው ኩዊር ሰዎች ራሳቸውን ማግለል መርጠዋል፣ ተደብቀዋልም።

በዛ ባለ የኩዊር ግሩፕ የሚታዩ አብዛኞቹ ጓደኞቼ ደህንነት ስለማይሰማቸው ወደትንንሽ ግሩፖች ተቀይረዋል። ወደውጪ መውጣት እና መገናኘት ትልቅ የአደጋ ስሜትን ይፈጥራል፤ አንድ ሁለት ቢራ መባባል ራስን የሌሎችን አይን ወደሚስብ ዳንስ እና ጨዋታ ተቀይሮ የተቃራኒ ፃታ አፍቃሪያንን ሊስብ ይችላል። ትንሿ ጥርጣሬ ወደአካላዊ ጥቃት እና ማስፈራሪያ እንደምትቀየር ስላየሁ እፈራለሁ። ስለዚህ በዛ ብሎ ከመሰብሰብ በየቤታችን እና በየጓደኞቻችን ቤት መዝናናትን መርጠናል። ጥቂቶቻችን የሸክላ ስራ ስልጠናን እና ዮጋ ስፖርትን አብረን መስራት ጀምራናል። ይሄም የአብሮነትን ስሜት በትንሹ ለመፍጠር የምናደርገው ጥረት ነው። እነዚህን ቦታዎች መምረጥ ከብዙ ስብስብ ይልቅ ከለላ ይሆነናል፤ ኢላማ ከመሆንም ይጠብቀናል።

የድሮውን ያለሃሳብ እና ፍርሃት የምንጨፍርበትን፣ የምንዝናናበትን ጊዜ በጣም እናፍቃለሁ። ብዙ ራሴን በሆኑ እና በሚረዱኝ ሰዎች ተከብቤ የነበረኝን የነፃነት ስሜት አስታውሳለሁ።

አሁን ላይ እኔም ከነዚህ ስብስቦች ራሴን ሳገል ይታየኛል:: ቢከብድም ተስፋዬ በትንሿ የጓደኝነት ስብስብ ውስጥ ነው። ምንም እንኳን ኢትዮጵያ የተመሳሳይ ፃታ አፍቃሪ ጠል ሃገር ብትሆንም በጥቂቱም ቢሆን ነፃ የመሆን ስሜት ነበረኝ፤ በእይታ ውስጥ ተደብቄ ነበር። አሁን ላይ ግን የእውነትም እንደተደበኩ ይሰማኛል እናም የመገለል ስሜት አለው። ይሄን ስሜት በጣም እጠላዋለሁ።

Leave a Reply

Discover more from queerethiopia

Subscribe now to keep reading and get access to the full archive.

Continue reading